ህዝቡን የሚያውኩ ከሆነ ከሰራዊቱ ጋር ይጣላሉ” ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

ህዝቡን የሚያውኩ ከሆነ ግን ከሰራዊቱ ጋር ይጣላሉ” ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

ጀነራሉ ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሁሉም ፓርቲዎች ሀሳባቸውን የመስጠት ፣ የመከራከር ፣ የተለያየ አማራጭ የማምጣት መብት አላቸው ፣ ፓርቲዎች ህገ መንግስት ይሻሻል፣ ፓርላማ ይበተን ፣ ህገ መንግስት ይተርጎም ፣ የሽግግር መንግስት ይመስረት፣ ባላደራ መንግስት ይቋቋም ሊሉ ይችላሉ ይህ ሁሉ ስራ ግን የፖለቲከኞች እንጂ የሰራዊቱ ስራ አይደለም ሲሉ ገልፀዋል

አንዳንዶች ሐምሌ ወር ምርጫ ማድረግ አለብን የሚሉም አሉ ይህን ማለትና መከራከር ይችላሉ እኛ እዛ ውስጥ አንገባም ስራችንም አይደለም ብለዋል።
ጀነራል ብርሃኑ የሰራዊቱ ስራ የህዝቡን ደህንነት በህገ መንግስት መሰረት መጠበቅ ነው ፤ በሰላም ወጥቶ እዳይገባ፣ ሰርቶ እንዳይበላ፣ የሚያስጨንቀውና የሚያንገላታው፣ የህይወቱን ዋስትና የሚያሳጣው ነገር እንዲፈጠር በፍፁም አንፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል።
‘በፖለቲከኛው እርግጫ ህዝቡ መረገጥ የለበትም’ ያሉት ጀነራል ብርሃኑ ፖለቲከኞች መደራደር ፣ መፎካከር ፣ መወያየት ፣ በሃሳብ መፋጨት ፣ ጎዳና ወጥተው ሰልፍ ማድረግ ፣ ተደራድረው ስልጣን መካፈል ፣ በሰላማዊ መንገድ ተወዳድሮ በማሸነፍ ስልጣን መውሰድ ይችላሉ ነገር ግን ህዝቡን የሚያውክ ነገር ካደረጉ ከሰራዊቱ ጋር ይጣላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ

About expeder

Check Also

Protest Letter againt Dereje Hawaz, Oromo activist working with OMN in USA

To: Schweizer Engineering Company 2350 NE Hopkins Court Pullman, WA 99163 – USA Subject: Request for …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

8 + 1 =