ከኢትዮጵያዉያን ማህበር በአዉሮፓ የተሰጠ መግለጫ ! Open Letter from Association of Ethiopians in Europe.


ከኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮጳ የተሰጠ መግለጫ

ለሚመለከተው፣ ሁሉ፣

ዋና ጉዳዩ: ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  ላይ ራሱን የኦሮሚያ ቤተክህነት ብሎ የሚጠራ ፣ የቀማኛና የወራሪ አደገኛ ቡድን ህገ-ወጥ ወንጀል መፈፀሙን በተመለከተ ነው።

ይህንንም  በኦርቶዶክስ እምነት  ልዑላዊ ተቋም ላይ የተፈፀመውን ህገወጥ ተግባርና ወንጀል አጥብቀን እናወግዛለን እንታገለዋለን።

ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነታችን መሰረት ከመሆኗም በላይ የሀገራችን የታሪካችንና የህዝባችን ብሎም የአለምም ግንባር ቀደም አበርክቶ ያላት ናት። ፊደልን ህግና ስርዓትን አብሮነትን የህዝብን መብት ማክበርን ለትውልድ ያስተላለፈችም ናት።

ፅንፈኞቹ እንደሚሉት የኦርቶዶክስ ክርስትና በአማራ በግድ ተጭኖብን ነው እንጂ አንፈልገውም ይሉና በሌላ ጊዜ ደግሞ የኦሮሚያን ኦርቶዶክስ ቤተክህነት ማቋቋም አለብን ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የሀሰት ተረት ፈጥረው የብዙ ነገዶችን የጋራ ርስት በማጭበርበር ከስምንት ክፍለሀገሮች በላይ ጠቅለው ኦሮሚያ የሚሉት ህገ-ወጥ ክልል ፈጥረው አሁንም የመሬት ወረራና መስፋፋቱን ቀጥለውበታል።

የመጨረሻው ግባቸው ኢትዮጵያ የምትባለውን አለም የሚያውቃትን ጥንታዊ ሀገር አፍርሰው በምትኩ እነሱ የሚያልሙትን ኦሮሚያ የሚባል ሀገር የመፍጠር ነው።

ይህንንም ህልማቸውን አንዱ ማሳያው ይህ የሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ የፈፀሙት የእምነትና የህዝብን ተቋም በጠባብ ቡድን የመጠቅለልና የአንድ ነገድ ተቋም ለማድረግና ብሎም የበላይ ለመሆን የሄዱበት ርቀትና ክህደት ማሳያ ነው።

ስለሆነም እኛ የዚህ ማህበር አባላት  በሰፊው ከተወያየን ቦሀላ የሚከተሉትን ዉሳኔዎች አስተላልፈናል::

1ኛ- መንግስት ለሕገ ወጦቹ የታጠቁ ጥበቃዎችን መድቦ ከሕጋዊው ተቋም ጥበቃ ስላነሳ ሕዝቡ በመንግስት ላይ ያለዉን እምነት እንዲያጣ ስለተደረገ ምእመናኑ የራሱን ደብር እንዲጠብቁ እንጠይቃለን::

ይህ ራሱን የኦሮሚያ ቤተክህነት ተጠሪ ነኝ ባይ ቡድን አንድ ጊዜ በእምነትተቋም ሌላ ጊዜ በቋንቋና በስንደቅ አላማ በመዝሙር ወዘተ ምክንያት እየፈጠረ ሀገርና ህዝብ በመበተን አላማ ላይ ከተሰማራ ቆይቷል። ስለዚህ የህዝብን ህይወትና ንብረት ተቋሞቹን መጠበቅና ማስጠበቅ የመንግስት ተቀዳሚ ግዴታና ሀላፊነት ስለሆነ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ላይ እርምጃ እንዲወስድ እናሳስባለን።

2ኛ- ለወደፊቱም ዘርፈ ብዙ ሰላማዊ ህዝብን በቁሙ መግደል ማፈናቀል ንብረቱን መዝረፍና በቡድን ሴትና ወንዶችን የመድፈር ወንጀልን ከመከሰቱ በፊት እንዲያስቆም እንጠይቃለን ::

3ኛ- ሌሎች የሰብአዊ መብት አስከባሪ ተቋማትም የተቋቋሙበት ዋና አላማ የህዝብን መብት ነፃነት ደህንነት መክበሩን መከታተልና እንዲከበር ጥረት ማድረግ ስለሆነ የግለሰቦችና የወል ንብረታቸውና ቅርሶቻቸውንም ጭምር እንዲከበር ጥረት እንዲያደርጉ ማሳሰብ እንወዳለን። ለሚመለከታቸው አለም አቀፍ ተቋማትም ማመልከትም ተገቢ መሆኑን ማሳሰብ እንወዳለን።

4ኛ- ለአማራ፣ ልጆች በተለይ ባንድም በሌላም መንገድ ከዚህ ቡድን ጋር ለምትተባበሩ ጉድጓዳችሁን እየማሳችሁ መሆናችሁን አውቃችሁ ከህዝባችሁ ከፋኖ ጋር በአንድ ላይ ቁሙና ህልውናችሁንና ተፈጥሯዊ  መብቶቻችሁን እንድታስከብሩ ጥሪ እናቀርባለን።

5ኛ- ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህ አደገኛ ዘረኛ አስተሳሰብ አደጋው ለናንተም እንደማይቀርላችሁ አውቃችሁ ከአማራ ህዝብ ጎን እንድትቆሙ ሀገራዊ ብሔራዊ ጥሪ በአክብሮት እናቀርባለን።

6ኛ- ኢትዮጵያዉያን የሚይዙትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ ለምን ተያዘ ብሎ ሰዎችን ማሰርና  ማጉላላት እንዲቆም እናሳስባለን  !

7ኛ- ማንኛዉንም ቋንቋ ወጣቶችን በማስገደድ ለማስተማር መሞከር ጥላቻን ስለሚያመጣ በፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዲሆን አጥብቀን እንገልፃለን::

8ኛ- በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን ሀገራችን የገባችበትን የመከራ ዘመን ለመቀልበስ እጅ ለጅ ተያይዘን እንድንሰራ ግንኙነታችንን እንድናጠናክር የትግል ጥሪ ማቅረብ እንወዳለን።

1. ለኢትዮጵያ ፓርላማ

2. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያናት

3.ለአማራ ማህበራት በአዉሮፓ

4.ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

5.ለአማራ ማህበር በአሜሪካ

6.ለአማራ ባለሞያዎች ማህበር

7.ለአማራ ማህበር በኔቫዳ

8.ለአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ (ሳንዲያጎ)

9.ለዋሽንግተን አካባቢ አማራ ማህበር

10. ለአማራ ማህበር በጆርጂያ

11. ለአማራ ኅብረተሰብ ቅርስ በሚኒሶታ

12. ለአማራ ማህበር በሲያትል

13. ለዳላስ አማራ ማህበር

14. ለአማራ ማህበር በቺካጎ

15. ለአማራ ማህበር በኮሎራዶ

16. ለአማራ ማህበር በሎስ አንጀለስ

17. ለአዲስ ድምፅ ራድዮ

18. ለመረጃ ቴሌቪዥን 

ግልባጭ በያሉበት

www.ethiodiaspora.net

e-mail: info@ethiodiaspora.net

Main Office: Frankfurt, Germany

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

5 + 4 =