የሃጫሉ አጎት ጨምሮ 5 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

ዛሬ [ረቡዕ] በአምቦ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሟቹን ድምጻዊ አጎትን ጨምሮ 5 ሰዎች መገደላቸውን ከቤተሰብ፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ቢቢሲ አረጋግጧል።

ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል።

የሃጫሉ ታናሽ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ሲናገር “አጎታችን ተገድሏል። በእድሜ ትልቅ ሰው ነው። ያሳደገን ነው። የአባታችን ወንድም ነበር” ብሏል።

ከሟቾቹ መካከል የአንዱ የሃጫሉ አጎት መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሶስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል።

“የአጎታችን ሚስት እግሯን ተመታለች፣ የአጎቴን ልጅ የሚያገባም እጁን ተመቷል፣ የእህታችን ባል እግሩ ተመቷል” ብሏል።

ሰዎቹ ላይ ጉዳት የደረሰው የድምጻዊ ሃጫሉን አስክሬን እንወስዳለን በማለት ወደ ቤት የመጡ ወጣቶች ጋር የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት መጋጨታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ሃጫሉ አምቦ እንዲቀበር የቤተሰብ ፍላጎት ነው።

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የጀግና አሸኛኘት እንደሚደረግለት ተገለፀ
ፌደራል ፖሊስ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት የተመታው መኪናው ውስጥ መሆኑን ገለፀ
ዛሬ ከሰዓት በፊት በአዳማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አምስት ሰዎች ሞቱ
የአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በጥይት ተመተው ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ወይም ሆስፒታል ሳይደርሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር አምስት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የከተማው ወጣቶች ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር በመሄድ አርቲስቱ መቀበር ያለበት አዲስ አበባ ነው በማለት ድምጻቸውን ማሰማታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከቤተሰቦቹ ፍላጎት ውጪ አስክሬኑን ወደ አዲስ አበባ እንወስዳለን በማለት ግርግር የፈጠሩ ሰዎች አንደነበሩም ከነዋሪዎች ተረድተናል።

የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ቀብር ነገ በአምቦ ከተማ እንደሚከናወን ተነግሯል።

source: bbc.com

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

68 − 63 =