የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ሕልፈት በሚመለከት ከኢትዮጵያዊያን ማሕበር በአውሮፓ የተሰጠ የሐዘን መግለጫ !

የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ሕልፈት በሚመለከት ከኢትዮጵያዊያን ማሕበር በአውሮፓ የተሰጠ የሐዘን መግለጫ !

የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ሕልፈት ፣ እኛ የኢትዮጵያዊያን ማሕበር በአውሮፓ ሕብረት አባሎች በታላቅ ሐዘን ሰምተናል ።
አርቲስቱ በለጋ ዕድሜው እንዲቀጠፍም የተቀነባበረና የተደራጀ የሐይል ጥቃት ስንዘራ መንስዔ ምክንያቱም እንደነበረ ከመንግሥት፣ከፀጥታው መሥሪያ ቤትና ከአቃቤ ሕግ መግለጫ ተረድተናል ።
አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በአስከፊው የሕወሓት አገዛዝ ዘመን በሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ የገዢውን መደብ አባሎች በቁም ያብረከረከ ዘፈን በማቅረብ የለውጡን ሐይሎች ሁሉ ያነቃቃ ኪነጥበባዊ አቅርቦቱን በድፍረት በማቅረብ ታሪክ የማይረሳውን ትዝታ ትቶልን አልፏል ።
በዚህም ጥርስ የተነከሰበትን አርቲስት ለመበቀል የጥፋትና የሽብር ሐይሎች ኢላማቸው አድርገው፣በውስጥ ቀልባሾችና በውጫዊ ጌቶቻቸው ሽርክናና ትዕዛዝ ሕይወቱን እንደቀጠፉት በታላቅ ቁጭትና ሐዘን እያስታወስን፣ የነዚህ የጥፋትና የሽብር የተደራጁ ሐይሎች ተቀዳሚ ኢላማም የሐገራችንን ሠላምና የሕዝባችንን አንድነት ማናጋትና የእርስበርስ ጦርነት በማስነሳት ሐገር የማፈራረስ እኩይ ተግባር መሆኑን በአፅንኦት እንረዳለን ።
ጀግናው የሐገራችን ሕዝብም የተሰነዘረውን የፈሪዎች የሽምቅ በትር አላማ በመረዳት፣በክፉም ሆነ በደግ ጊዜ የሚያደርገውን መተሳሰብና አብሮ የመቆም ድንቅ ባሕሉን መሠረት አድርጎ ዛሬም የተቃጣበትን የጠላት በትር ተቋቁሞ በድል እንዲወጣ ከማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥትና ከፀጥታ ሐይሎቻችን ጎን ቆሞ እንዲመክት ጥሪያችንን እያቀረብን ፣ የሐገራችንን አንድነትና የሕዝባችንንም ሠላም ለማረጋገጥ ከመንግሥትና ከሕዝባችን ጎን የተሠለፍን መሆኑን በቁርጠኛነት እንገልፃለን ።
በመጨረሻም ለአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰቦች ዘመድና ወዳጆች እንደሁም ለመላው የሐገራችን ሕዝብ መፅናናትን እየተመኘን ሐያሉ አምላካችን የሀጫሉን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኖርልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

የኢትዮጵያዊያን ማሕበር በአውሮፓ ሕዝብ ግንኙነት !
www.ethiodiaspora.eu

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

+ 14 = 17