26.06.2020 የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ቃለ ጉባዔ የኢማአ የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ የመጀመሪይውን ስብሰባ አካሂዷል:: የስብሰባ ቦታ :- ፍራንክፈርት የስበሰባው ፈጻጸም :- በዙም በይነ-መረብ አገልግሎት የመነጋገሪያ ርዕስ:- የማህበሩን የአመራር አባላት የስራ ድርሻ ስለማደላደል ሰብሳቢ አቶ ሊሻን ግዛው ቃለ ጉባዔ ያዥ አቶ ማሞ ይሁኔ በአቶ ሊሻን ግዛው ሰብሳቢነት በተካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ ሥራ ለማስጀመር ብመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት የአመራር አባላት መሃከል የስራ ክፍፍል ማድረግና የሥራ እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት የአለቱን ስብሰባ ከፍተዋል:: በስብሰባው ላይ የተገኙት የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት በሂደቱ ላይ ምክክር በማድረግ የሚከተለውን ወስነዋል:: 1. የስራ አስኪያጅ ኮሚቴውን አባላት መምረጥ 2. ማህበሩን በህጋዊነት ለማስመዝገብ 7 ዝቅተኛ አባላት ስለሚያስፈልግ ተጨማሪ አባላትን መመልመና ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል:: የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት ምርጫ አሁን ባለው የአባላት ብዛት በደንቡ ውስጥ በጸደቀው የሥራ ሃላፊነት በሙሉ መሸፈን ስለማይቻል በአምስት የስራ ድርሻዎች ብቻ የሥራ ክፍፍል እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል:: በዚሁ መሰረት በተሰጠው ድምጽ የሚከተሉት የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል:: 1. ሊቀመንበር :- አቶ ሊሻን ግዛው 2. ም/ሊቀመንበር አቶ ጸደቀ ሀብተገብሬል 3. ዋና ጸሀፊ አቶ ዓለሙ ደጀኔ 4. ገንዘብ ያዥ -------------------- 5. የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደረጄ መንገሻ 6. የሂሳብ ሹም------------------------ 7. የማስታወቂያ ኦፐሬሽን ሃላፊ------------------- ከላይ ሰው ያልተመደበባቸው በቅርቡ በአዳዲስ ሰዎች እንዲሞሉ እቅድ ተይዞላቸዋል:: የማህበሩን ስራ ለማቀላጠፍና አሳታፊነቱን ለማረጋገጥ ከአውሮፓ አገሮች ርንጫፎች የሚወከሉ ባሉት የሥራ ዘርፎች ምክትል ሃላፊዎች ሆነው እንዲመደቡና የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴውን ስራ እንዲያጠናክሩት ስምምነት ላይ ተደርሷል::ይህም ሃሳብ በ 27.06.2020 እንዲቀርብና ተፈጻሚ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል :: በዚህ የሥራ አስኪያጅ ኪሚቴ የመጀመሪያ ስብስባ ስለ ማህበሩ መመስረት መግለጫ እንዲወጣ ውይይት ከደረገበት በኋላ በ27.06.2020 በሚካሄደው ጠቅላላ ስብሰባ እንዲቀርብና ውሳኔ እንዲሰጥበት ተወስኗል:: የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ለወደፊት ማህበሩ ሊጠናከርባቸው በ ሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ል ውውጥና ሰፊ ምክክር በማድረግ በፍጹም መግባባት የ ዕለቱን ስብሰባ ኣጠናቋል::