ጃዋር መሀመድ ስልክና ሬዲዮ ሲጠልፍ መንግስት የት ነበር?

ጃዋር መሐመድ እስካሁን ስልክ እና ኢሜል ጠልፎ ትላንት ሲናገር ፖሊስ የት ነበር!?

ከቴሌ እውቅና ውጭ የሚሰራ የሳተላይት መቀበያ ጃዋር መሐመድ ቤት ውስጥ መገኘቱን ከፖሊስ እንደሰማ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ሪፖርተር የጠቀሰው ፖሊስ ጃዋር መሐመድ በአንደበቱ ከወራት በፊት አገር ቤት ካለ አንድ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሰዎች በስልክ የሚያወሩትንና በኢሜል የሚጻጻፉትን በመጥለፍ ሚስጥራዊ መረጃ እንደሚሰበስብ በአደባባይ የተናገረውን አልሰማም ነበር? የሰዎችን የስልክና ኢሜል ግንኙነት እንደሚጠልፍ ለማረጋገጥም የዳንኤል ክብረትን ኢሜል በመስበር ዳንኤል በኢሜል ሲልክ እጅ ከፈንጅ ያዝነው በማለት “Confidential” የሚል መግለጫ ያለውና የዳንኤል ክብረት ስም ያለበት ሚስጥራዊ ሰነድ በፌስቡክ አካውንቱና በሚቆጣጠረው በፊንፊኔ ኢንተርሰፕት ለጥፎ እንደነበር ፖሊስ አላየም፤ አልሰማም ማለት ነው? የጥቅምቱን ፍጅት ተከትሎ ዐቢይ አሕመድ ሐረር በመገኘት በኦሮምኛ ባደረገው ንግግር “ጃዋር መሐመድ ተለዋጭ መንግሥታችን ነው” ሲል ሁለተኛ መንግሥትነቱን ያረጋገጠለት ጃዋር መሐመድ ግለሰብ ሆኖ ሳለ ሰዎች በስልክ የሚያወሩትንና በኢሜል የሚጻጻፉትን በመጥለፍ ሚስጥራዊ መረጃ እንደሚሰበስብ በአደባባይ ሲናገር ፖሊስ ተብዮው ጃዋርን ያልጠየቀው ጃዋር ስልክና ኢንተርኔት የሚጠልፈው በሳተላይት መቀበያ ሳይሆን በሜንጫ ይሆናል ብሎ ስላሰበ ይሆን¡¿ ጃዋር የሰዎችን ስልክና ኢንተርኔት ሲጠልፍበት የነበረውን ሳተላይት መቼ እና በማን ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገባ በወቅቱ የጉሙሩክ ገዢ የነበረችው አዳነች አበቤስ አታውቅም ማለት ነው?

አቻምየለህ ታምሩ

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

76 − = 75