Ethiopians in Europe support Ethiopian unity !

በሕወሓትና ተባባሪዎችዋ አስከፊ የአገዛዝ ዘመን ፣ በወገናችን ላይ ይደርስበት የነበረውን የማሕበራዊ ፍትሕ መዛባትንና ሌሎች ዘርፈ ብዙ በደሎችን በረጅምና እልህ አስጨራሽ ውስብስብ ሠላማዊ ትግል አስጨንቆ በመያዝ በሥርዐቱ በራሱ ውስጥ ለነበሩት የለውጥ ፋና ወጊ ሐይሎች መንገድ በመክፈት የሕወሓትን አምባገነናዊ ሥርዐት ቁንጮ ማፍያ መሪዎች ከመሐል ሐገር አፈግፍገው በራሳቸው ክልል ወሸባ እንዲገቡ አስገድዷቸዋል።
በዚህም አዲስ ክስተት የተነሳ በተፈጠረው የለውጥና የመነሳሳት መንፈስ በመቃኘት ” ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን” የሚለው የአባቶቻችን ታላቅ ኢትዮጵያዊ የመነሳሳትና ድል አድራጊነት መንፈስ በመላው የሐገራችን ምድር እንዲሰፍን አድርጎታል ።
በዚህም የተነሳ የለውጡ ሐይሎች ምንም እንኳን የዘመናት የወገናችንን ራዕይ ዕውን ለማድረግ ብዙ ተጨባጭና ጉልህ እርምጃዎችን ቢወስዱም ቅሉ ተፃፃራሪ የውስጥ ሐይሎችና የአካባቢ ፀረ ኢትዮጵያ ሐይሎች የጋራ ግንባር በመፍጠር ተሸናፊውን ጎጣዊ አገዛዛቸውን መልሰው በሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለመጫን ቀን ከሌት ሲቧችሩ እያየን ነው ።
በተለይም በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ሐብት እየተሠራ ያለውን የታላቁን የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ለማደናቀፍና በግድቡ የምናገኘውን የሐይል አቅርቦት በማጨናገፍ የተለምነውን ሁለገብ የእርሻና የእንዱስትሪ ዕድገት ራዕይ ለማጨለም እየተራወጡ ይገኛሉ ። ይህ ከግብፅ ዘመናዊ ፈርኦኖች አንስቶ እስከ ጊዜያችን የውስጥ አርበኞችና ሥልጣን ናፋቂ የጎጥ ቆሮዎቻቸው ድረስ የዘለቀ የጥፋት ሐይል ፣ በአንድ የጋራ ግንባር የተቀናጀና በስልት የሚንቀሳቀስ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ዕድገት አጥፊ የሸሪኮች ስብስብ ነው ።
የዚህንና የሌሎች ሐገራዊ አደጋዎችን ጥፋት ታላሚ በማድረግ እኛም በአውሮፓ የምንኖር ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሐገራችንና ሕዝባችንን ለመታደግና የዜግነት ግዴታችንንም ለመወጣት ” የኢትዮጵያዊያን ማሕበር በአውሮፓ ( ኢማፓ) የተሰኘ የአብዛኛው የአውሮፓ ሐገሮች ተወካዮች የተሳተፉበት የረጅም ጊዜ ውይይትና ተግባቦት ፍሬ የሆነ ማሕበር በማቋቋም ከሕዝባችንና ከለውጡ ጎን የተሰለፍን መሆኑን በይፋ እናስታውቃለን !
ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን !
ኢትዮጵያ በልጆችዋ ሕብረት ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች !

Association of Ethiopians in Europe has been established !

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

2 comments

  1. i am ethiopian in poland. How can i become member?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

37 + = 45