ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጥሪን ተቀብለው የሚመጡ እንግዶቹን ለመቀበል ተዘጋጅቻለሁ አለ!

ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ “ 1 ሚለየን ወደ አገር ቤት “ ጥሪን ተቀብለው የሚመጡ እንግዶቹን ለመቀበል ተዘጋጅቻለሁ አለ::

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንግዶቹን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ገለፁ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።

በዚሁ መሰረት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የታደሰም ሆነ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት መታወቂያ ያላቸው፥ እንዲሁም በልዩ ሁኔታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተጓዦች የታደሰም ሆነ ጊዜው ያለፈበትን መታወቂያ አውሮፕላን ማረፊያ በኢሚግሬሽን ካውንተር ላይ ስለሚጠየቁ በእጃቸው ሊይዙ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሌላ አገር ፓስፖርት የያዙና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊ ሰነዶችን በማዘጋጀት http://xn--www-86o.digitalinvea.com/ድረ ገጽ ላይ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ በፊት የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የሌላቸው ደንበኞች ፥ የቪዛ አገልግሎት ለማግኘት በ www.evisa.gov.et ድረ ገጽ ላይ በማመልከት በሂደቱ ለሚያጋጥማቸው ችግር support@evisa.gov.et በሚል የኢሜል አድራሻ ላይ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችሉም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።

ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ አገር ቤት ለሚገቡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመዳረሻ ቪዛ /on arrival visa/ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

የቪዛ ጥያቄ በተቋሙ ህጋዊ ድረ ገጽ www.evisa.gov.et ላይ ብቻ እንደሚሰጥም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

About expeder

Check Also

Letter to Ambassador of the United States in Ethiopia

May 18, 2024 The Honorable Mr. Ervin Massinga Ambassador of the United States to Ethiopia U.S. …

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

+ 43 = 45