የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ የመተዳደሪያ ደንብ – ByLaw of Association of Ethiopians in Europe
ምዕራፍ አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
አንቀጽ1. ስያሜ
ይህ ማህበር “የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ” ወይም ኢ.ማ.አ. (A.E.E.) ተብሎ ይጠራል።
አንቀጽ 2 አድራሻ፣መቋቋምና ተልእኮ
2.1.የማህበሩ ዋና አድራሻ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ነው።
2.2. ማህበሩ በመላው አውሮፓ ቅርንጫፎች (chapters) ይኖሩታል::
2.3.ማህበሩ በአውሮፓ የማህበራት ህግና ደንብ መሰረት ማህበራዊ ዓላማዎችን ብቻ ተግባራዊ የሚያደርግ ድርጅት ነው::
2.4.የማህበሩ ንብረት የማህበሩን ህገደንብ የሚያክብሩ ዓላማዎችን ማስፈጸሚያ ብቻ ይውላል::
2.5.ማህበሩ ከማንኛዉም ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ዉጪ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ የጎሳና የሃይማኖት ድርጅቶችና ማህበራት ገለልተኛ ነው::
2.6.ማህበሩ በአውሮፓ ሕግ መሰረት ተቋቁሞ፣ ለትርፍ የማይሰራ ማህበር ነው።
2.7.ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።
ምዕራፍ ሁለት
አንቀጽ 3 ዓላማ:.
3.1 የዜጎች ሠብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ሙሉ በሙሉ የተከበሩባት የህግ ልዕልና እንዲረጋገጥ መታገል::
3.2 በዜጎች መሃል እኩልነት እንዲሰፍን፣ የእያንዳንዱ ዜጋ መብት እንዲረጋገጥ፣ መተማመን እንዲጎለብት ለጋራ አገር በጋራ መቆም እንዲጠናከር መስራት::
3.4 መንግስት የህዝብንና አገርን አደራ በመቀበል የዜጎችን እምባ የሚያብስ የእድገት መሰላል ሆኖ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰራ ለማበረታታት::
3.5 ዜጎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች በጋራ እንዲገነቡ፣ እንዲጠብቁና እንዲያስከብሩ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመስጠት::
3.6 በውጭ አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በዘርና በሃይማኖት ሳይከፋፈል የህዝባችን ቋሚ ደጀን በመሆን ለአገራዊ እድገታችን በጋራ እንድንሰራና የሚቻለንን አስተዋጽኦ ለማድረግ::
3.7 በኢትዮጵያ ፈጣንና ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ፣ የሃብት ፍሰት፣የእውቀት ሽግግርና የተክኖሎጂ ውጤቶችን ለማቅረብ ጥረት ማድረግ ::
3.8 ዜጐች ለሀገራቸው ፍቅር እንዲኖራቸው፣ ለጋራ እድገታቸው በተባበረ ጉልበት፣ እውቀት፣ ለዘላቂና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲሰሩ ለማበረታታት::
3.9.ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የነገ አማራጭ፡መንግስት የመሆን እድሉን ለማግኘት ህዝብን በጎጥ የመከፋፈል መርዝን ከመርጨትና እልቂትን ከመደገስ ተቆጥበው በታላቅ አገራዊ የሃላፊነት መንፈስ እንዲራመዱ ለማበረታታት::
3.10 ፍትሃዊ ምርጫ ብቸኛው የስልጣን ቅብብሎሽ መሆኑን በመቀበል ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ተደማምጠውና ተከባብረው ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲሰሩ በተፈተኑ የዓለማችን ተሞክሮዎች ለማገዝ ::
3.11 የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በራሱና በወረሰው መልካም ነገር የኩራት መንፈስ እንዲያዳብር ጥረት ማድረግ፣ የነገ ተስፋውን በሚያጨልሙ የዘር ቡድኖች ተከፋፍሎ ከመናቆር ተቆጥቦ እራሱን በእውቀትና ክህሎት በማነጽ፣ የበለጸገች ደሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመፍጠርና የአገር ተረካቢነቱን ተልኮ በክብር እንዲወጣ ለማደፋፈር::
3.12 የአባይን ግድብና ሌሎች ተፈጥሮአዊ ሃብቶቻችንን መጠቀም ልዑላዊ መብታችን በመሆኑ በማንም ለድርድር እንዳይቀርቡ ተባብሮ ለመስራት የዕውቀት የገንዘብ የቁሳቁና የድፕሎማሲ ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠት::
3.13 ሚዲያ የመረጃ ምንጭ እንደመሆኑ የድምጽ የሕትመት የምስል ተቋሞቻችን ና በመስኩ የተሰማሩ ጋዜጠኖችና ባለሞያዎች ለማንም ያልወገነ እውነተኛ የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑና አገርን ከጥፋት ህዝብን ከ እልቂት እንዲታደጉ ለማስቻል ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠት::
3.14 በዲያስፖራ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሳንክፋፈል እኔም በአገሬ ጉዳይ ያገባኛል መንፈስ ሁለንተናዊ አቅሞቻችችን በማስተባበር ለኢትዮጵያችን እንድናበረክት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ::
3.15 አገራዊ አንድነትዋ የተጠበቀ የህዝቦቿ ልዑላዊነት የተረጋገጠ፣ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ ጠንካራ ማህበራዊ ኢኮኖሚ የተገነባባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚካሄደውን ትግል ለማገዝ::
ምዕራፍ ሶስት
አንቀጽ 4 ተግባር
የማህበሩ ተግባራት
4.1 ማህበሩ ለማህበራዊ፣ ለባህላዊና ሰብዓዊ ዓላማዎች የቆመ ሲሆን በአንቀጽ 3 የተጠቀሱትን አላማዎች ለማሰፈጸም የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል::
4.2 ማህበሩ የኢትዮጵያን ህዝብ የተለያዩ ባህላትና ቋንቋዎች ወግና ጥሩ ልምዶች በአውሮፓ ህብረት አገሮች በማስተዋወቅ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው አገሮች በንቃት እንዲሳተፉ ይሰራል::
4.3 በአውሮፓ ከሚገኙ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማህበራትና የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመገናኘት ለኢትዮጵያ አገራችን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ይጥራል፣..
4.4 በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ን በማስተባበር በአገር ውስጥ እየተካሄደ ላለው የአገር ግንባታ የሞራል ፣ የፋይናንስ ፣የቁሳቁስ እርዳታና የዕውቀት ሽግግግር ንቁ ሆነው እንዲሳተፉ ማድረግ
4.5 የማህበሩ የገንዘብና የዝግጅት ኣቅም በፈቀደ ጊዜ የኢትዮጵያንና ታሪካዊና ሃይማኖታዊ በዓላትን በማዘጋጀት ህብረተሰቡ ተሰብስቦ በጋራ እንዲያከብር ያደርጋል::
4.6 የማህበሩ የኣባላት ኣቅም ሲዳብርና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ የተለያዩ ዘርፎች ኮሚቴዎችን ያደራጃል::
4.7 በኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋዎች (የዉሃ መጥለቅለቅ የድርቅ የመሬት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት) ሲደርሱ ማህበሩ የኢትዮጵያንና የአውሮፓ መንግስታትን ፣መንግሥታዊ ያልሆኑ የግልና የቤተክርስቲያን እርዳታ ሰጪ ድርጀቶችን በማስታባበር እርዳታ ለማሰባሰብ ይጥራል:: የማህበሩ የገንዘብ አቅም ከፈቀደ ከካዝናው የገንዘብ እርዳታ ይለግሳል::የሚለገሰው መጠን የሚወሰነው በጠቅላላ ጉባዔው ነው::
4.8 ማህበሩ በኢትዮጵያ፣ በአውሮፓና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የሰባዊ መብት አስከባሪ ደርጅቶች ከአዉሮፓ ህብረት ባለስልጣኖችና የፓርላማ አባላት ጋር ግንኙነት ይፈጥራል::
ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብዓዊ መብት በሚጣስበት ጊዜ ማህበሩ ከላይ ለተጠቀሱት ድርጅቶች ሁኔታውን ያስታውቃል::
ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል፣ ፊርማዎችን ያሰባስባል ጋዜጣዊ መግለጫዎችንም ይሰጣል::
4.9 በአውሮፓ ውስጥ ህገወጥ ድርጊቶችና በዘረኝነት መንፈስ ተነሳስቶ የሚፈጽም ጥቃት ሲፈጸም ከሰብዓዊ ደርጅቶች ጋ በመተባበር ከጋዜጣዊ መግለጫ እስከ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ድረስ የሚዘልቅ እንቅስቃሴ ያደርጋል::
4.10 የማህበሩ የገንዘብና የሰው ሃይል ኣቅም ሲፈቅድ የማህበሩ ኣባላትና ኢትዮጵያዉያን የሚሳተፉበት በራሱ ስም መጽሄት ያዘጋጃል፣ መጽሄቱ የሚወጣበትን ጊዜ ኣንደኣስፈላጊነቱ ይወሰናል::
4.11 ማህበሩ በወቅታዊ የአገራችንና የዓለም ዓቀፍ ሁኔታዎች ዙሪያ ሴሚናሮች፣ የኮንፈረንሶችንና ሲምፖዚዬሞችና መድረክ በማዘጋጀት የኢትዮጵያዉያንና የጀርመን (አውሮፓ ሕብረት) የፖለቲካ፣ የታሪክና የኢኮኖሚ ምሁራን፣ ሌሎች ባላሙያዎችና የሙያ ማህበራት ተወካዮችን ወዘተ. ጋብዞ በጀርመን(በአውሮፓ ሕብረት) የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሃገራቸዉና በጀርመን ሃገር ስላለዉ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያዉቁና ኣመለካከታቸዉን እንዲያዳብሩ ያደርጋል::
4.12 ማህበሩ በአገራችን የሚከናወናውን ለውጥ እየተከታተለ የተሻለ ነገር ሲሰራ በማድነቅ ጥፋቶች ሲታዩ አመራሩ እየገመገመ መግለጫ ይሰጣል፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ያወጣል::
ማህበሩ ኢትዮጵያ የምታደርገዉን የዲሞክራሲና የኢኮኖሚ ግንባታ ይደግፋል::
4.13 ማህበሩ ዓላማዎችን ለማሰፈጸም እንዲረዳው የዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም ድረገጽ ፣ማህበራዊ ሳይቶችን ያደረጃል ፣አቅም በፈቀደ መጠን የድምጽ ፣ የምስልና የህትመት ውጤቶችን ያሰራጫል::
4.14 የመረጃ አያያዝ ቅርፆችን መቅረጽ ፣ የተደራጀ መረጃ በወቅቱ እና በአግባቡ መያዝ፣ መሰረታዊ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት::
4.15 ለማህበሩ አባላት በየወቅቱ መረጃ በማስተላለፍ ተሳትፎቸውን የማሳደግ የውቀትና የልምድ ሽግግርን ማጠናከር።
4.16 በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ዴሞክራሲያዊ የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀፍ የለውጥ ኃይሉ የሚያደርጋቸውን ክንውኖች በተግባር ማበረታታትና በሚቻለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያገኝ መርዳት::
4.17 የአባይ ግድብ ግንባታ የአገራችን ዘላቂ እድገት ዋስትናችን በመሆኑ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንኖር ዜጎች እጅ ለእጅ ታያይዘን ሁለንተናዊ ድጋፍ ያገኝ ዘንድ የተጠናክረ ስራ መስራት::
ታሪካዊ አሻራችንን በማኖር የዜግነት ግዴታን በክብር ለመወጣት መንቀሳቀስ።
4.18 የአባይ ግድብ እንዳይሳካ የግብጽ መንግስትና የዐረብ ሊግ የልማት ጎዞአችንን ለማደናቀፍ የሚሸርቡትን ደባ ሴራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማጋለጥ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ!
ምዕራፍ አራት
አንቀጽ 5. አባልነት
5.1 አባል ስለመሆን፣
5.1 በአውሮፓ አህጉር የሚኖር ዕድሜው 18 በላይ የሆነ፣ለህጋዊ ተጠያቂነት የሚበቃ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣
5.2 የማህበሩን ደንብና ሕግ የተቀበለና ለማህበሩ ዓላማዎች ተግባራዊነት የሚቆም ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል።
5.3 ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋብቻና በማደጎ ትስስር ያላቸው የሌላ ሀገር ዜጎች የክብር አባል መሆን ይችላሉ::
5.4 የማህበሩን የክብር አባላት ከመምረጥና ከመመረጥ በስተቀር በሌሎች የአባልነት መብቶች ላይ ሁሉ እኩል ተጠቃሚ ናቸው:
5.5 ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት የቆመና የተለያዩ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ክፍሎች ተባብረውና ተከባብረው በሰላም አብሮ መኖርን የሚቀበል ፣
5.6 በአውሮፓ ዉስጥ በወንጀለኝነት የማይፈለግ ወይም በህገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ከሚሰበስቡ ድርጅቶች ዉስጥ የማይሳተፍ፣ ተከሶ ያልተቀጣና በወንጀል የማይፈለግ (የማትፈለግ) በኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ አባል መሆን ይችላል ወይም ትችላለች::
5.7 አንድ ሰዉ የማህበሩ አባል መሆን የሚችለው በማህበሩ ምስረታ ላይ ሲገኝ ወይም የአባልነት ቅጽ ሞልቶ ሲያመለክት ብቻ ነው:: የአባልነት ማመልከቻው ተሞልቶ ለማህበሩ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጽሁፍ መቅረብ አለበት:: አባልነቱ የሚረጋገጠው የማህበሩ የአመራር ኮሚቴ ወስኖ የማህበሩን ህገ ደንብ አባሪ አድርጎ በጽሁፍ ለአመልካቹ ሲልክለት ብቻ ነው:: የአባልነት ማመልከቻው ዉድቅ ከሆነ አመልካቹ ጽሁፉ በደረሰው በአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ ይኖርበታል:: የአመራር አካሉ ማመልከቻውን ዉድቅ ያደረገበትን ምክንያት መስጠት አይገደድም:: የአመራር ኮሚቴው የይግባኙን በጽሁፍ ለሚከተለው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል::
5.8 ከአዉሮፓ ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዊ የድያስፖራ አባላት በታዛቢነት የመሳተፍ ሃሳብ የመስጠት የመወያየት እድል አላቸው::
5.9 የማህበሩ አባል ለመሆን በድህረ ገፃችን ላይ የሚገኘዉን የአባልነት ቅፅ መሙላት አስፈላጊ ነው ። www.ethiodiaspora.net/membership
ኣንቀጽ 6 የአባላት መብት
6.1 ማንኛዉም ኣባል በማህበሩ ህገ ደንብ ዉስጥ የተደነገገለትን መብት መጠቀም ይችላል. በተለይም በጠቅላላ ጉባዔዉ ተካፍሎ በዉይይት አርእስቶች ላይ የመወሰን መብት ኣለዉ.
6.2 የማህበሩን የአመራር አካላት የመምረጥና በነሱ ዉስጥ የመመረጥ መብት አለው:: አባሉ በማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም በተለያዩ ማህበራት ወዘተ. የአመራር አካል ከሆነ በማህበሩ የአመራር ኮሚቴ ዉስጥ መመረጥ አይችልም::
6.3 ማንኛዉም አባል በማህበሩ ንብረቶች የመጠቀምና በማህበሩ የእንቅስቃሴ ህይዎት የመካፈል መብት አለው::
6.4 ማንኛዉም አባል የጠቅላላ ጉባዔና የስራ ኣስኪያጅ ኮሚቴ ዉሳኔዎችና ድንጋጌዎችን መዛግብት የማህበሩ ዋና ጸሃፊ በተገኘበት ማየትና ማንበብ ይችላል:: መዛግብትንና መረጃዎችን ወስዶ በማራባት ለአባላትና አባል ላልሆኑ ግለሰቦች ማሰራጨት ግን በማህበሩና በጀርመን (የአውሮፓ) ህገ ደንብ መሰረት ፍጹም ክልክል ነው::
6.5 ማንኛውም አባል ማህበሩ ስበሳብውን የሚያካሂደበትንም ሆነ ወደ ድህረ ገፁ የመግቢያውን ቁልፍ ወይም( Password) የማህበሩ አባል ላልሆነ ሰው ሰጥቶ ቢገኝ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ሊወሰድበት ይችላል::
6.6 ማንኛዉም አባል ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች ላይ በነጻ የመሳተፍ መብት አለው፣ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች ላይ የስራ አመራሩ የመግቢያ ክፍያ ከተመነ ግን በነጻ የመሳተፉ መብት ውድቅ ይሆናል::
6.7 አባል የሆነ ወገናችን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ለመስራት ለመነገድ ወይም እርዳታ ለማድረግ ችግር ቢያጋጥመው ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ችግሮችን ለመፍታት ማህበሩ ይጥራል::
አንቀጽ 7 የኣባላት ግዴታ
ማንኛዉም አባል የሚከተሉትን ግዴታዎች ሟሟላት ይጠበቅበታል
7.1 የማህበሩን ህገ ደንብና ዉሳኔዎቹን ማክበር
7.2 የማህበሩን ዓላማዎች ማስፋፋትና ማጠናከር
7.3 የጠቅላላ ጉባዔና የአመራር ኣካል ዉሳኔዎችን ማክበርና በስራ ላይ ማዋል
7.4 የአባልነት መዋጮውን በወቅቱ መክፈል
7.5 የማህበሩን እንቅስቃሴዎች በትጋት መስራትና ማጠናከር
7.6 እያንዳንዱ አባል ራሱ ስለሚናገረው ወይም ስለሚፅፈው ጉዳይ ተጠያቂው ራሱ ግለሰቡ ነው::
ኣንቀጽ 8 የኣባልነት መዋጮ
8.1 ማንኛዉም አባል የማህበሩን የአባልነት ወርሃዊ መዋጮ የመክፈል ግዴታ አለበት. የመዋጮው መጠን በጠቅላላ ጉባዔው ተመርምሮ ከወቅቱ ጋር በማጣጣም ይወሰናል::
በኣሁኑ ጊዜ ወርሃዊ መዋጮዉ 5€ እንዲሆን ተወስኖአል::
8.2 የአባልነት መዋጮው ቢያንስ በ3 ወር ዉስጥ መከፈል አለበት:: የአባልነት ክፍያ በየግማሽ አመቱ ወይም በየአመቱ መክፈል ይቻላል:: መዋጮው ቢያንስ በ3ኛዉ ወር መጨረሻ ላይ መከፈል አለበት::
ኣንቀጽ 9 ከማህበሩ ኣባልነት ስለመውጣት
9.1 ማንኛውም አባል ከማህበሩ ኣባልነት በማንኛዉም ጊዜ መሰናበት ይችላል::
9.2 አንድ አባል ከማህበሩ ሲሰናብት ከመሰናበቻው ቀን በፊት የ 4 ሳምንታት የጊዜ ገደብ ሰጥቶ ለማህበሩ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጽሁፍ ማስታወቅ አለበት::
የስንበት ደብዳቤው ህጋዊ የሚሆነው እስከ መሰናበቻ ቀኑ ድረስ ያለበትን የማህበሩን ወርሃዊ መዋጮ አጠቃሎ ሲከፍል ብቻ ነው::
9.3 ማንኛዉም አባል የመሰናበቻ ጽሁፍ ሳያቀርብ በሌሎች ምክንያቶች ከማህበሩ ከወጣ ተመልሶ አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበ በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ታይቶ ይወሰናል::
ኣንቀጽ 10 ከማህበሩ ኣባልነት ስለመወገድ
10.1 ማንኛዉም አባል በሚከተሉት ምክንያቶች ከማህበሩ ሊወገድ ይችላል.
10.2 የማህበሩን ህገ-ደንብ ጥሶ የማህበሩን ጥቅምና እንቅስቃሴ የሚጻረር ተግባራትን መፈጸሙ በማስረጃ ሲረጋገጥበት
10.3 በማህበሩ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶ ሲገኝ
10.4 የመተዳደሪያ ደንቡን ተከትሎ: ግልፅነት በተሞላበት መልኩ በማህበሩ አባላት በድምጽ ብልጫ የሚጸድቁ ተግባራትን ባለመቀበል በስርአት አልበኝነት፣ ፀብ አጫሪነትና ረብሻ ብጥብጥ የሚያስነሳ ማንኛውም አባል ለአጭርም ሆነ ለረዥም ግዜ ከማህበሩ ሊታገድ ወይም ከማህበሩ ሊሰረዝ ይችላል::
10.5 እምነትን ሲያጎድልና ማህበሩን ያለአግባብ ሲጠቀምበት ሲገኝ፣
10.6 የወራት የአባልነት መዋጮውን ሳይከፍል ቀርቶ ሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂየ ደርሶት ያለበትን ውዝፍ አጠቃሎ ካልከፈለ፣
10.7 አባላትን የሚሳደብ የሽብር ወይም ሐሰት ዜናዎች ደጋግሞ የሚያስተለልፍ የሀገራችንን አንድነት የሚፃረር የሚናገር አባል ከማህበሩ ይወገዳል::
10.8 ከዚህ አለም በሞት ሲለይ::
ምዕራፍ አምስት
ኣንቀጽ 11 የማህበሩ የአመራር አካላት
ማህበሩ የሚከተሉት የሥራ አመራር አካላት አሉት
11.1 ጠቅላላ ጉባዔ
11.2 የስራ አስኪያጅ (Executive) ኮሚቴ
11.3 የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተሮች) ኮሚቴ
11.4 የዲስፕሊን ኮሚቴ
11.5 የተለያዩ የንኡሳን ኮሚቴዎች
11.6 የዉይይት መድረክ አስተዳዳሪዎች (Admins)
ኣንቀጽ 12 ጠቅላላ ጉባዔ
ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ የበላይ አካል ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራትን ያከናውናል::
12.1 ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴ የሚቀርቡትን የአመት በጀት ያጸድቃል፣ ይወስናል::
12.2 የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አመታዊ የስራ ሪፖርት ያዳምጣል የስራ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል መመሪያ ይሰጣል::
12.3 የስራ አስኪያጅ ኮሚቴን ያሰናብታል::
12.4 ወቅቱን የተከተለ የአባልትን ወርሃዊ መዋጮና የመመዝገቢያ ተመን ይወስናል::
12.5 የስራ አስኪያጅ፣የቁጥጥር ና የሂሳብ መርማሪ ኮሚቴ አባላትን (ኦዲተሮችን) ይመርጣል::
12.6 የአባልነት ማመልከቻቸዉ ዉድቅ የሆኑ ኣመልካቾች ይግባኝ ላይ ዉሳኔ ይሰጣል::
12.7 ማህበሩ በኢትዮጵያ ለሚደርሱ የተፈጥሮ ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚሰጠዉን የእርዳታና የድጋፍ መጠን ይወስናል::
ኣንቀጽ 13 የጠቅላላ ጉባዔ ኣጠራርና ዉሳኔ አሰጣጥ
- የጠቅላላ ጉባአዔ ዉሳኔ በአንድ ድምጽ ብልጫ ይጸድቃል::
13.1. የማህበሩ ጉባዔ ድምጽ አሰጣጥ እኩል ከሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ውሳኔ ተፈጻሚነት ይኖረዋል::
13.2 የማህበሩን ህገ ደንብ ለመለወጥና ማህበሩን ላማፍረስ ግን በኣባልት ¾ ድምጽ መደገፍ አለበት::
13.3 የአባላቱ 1/10 ኛ የማህበሩ አባላት ምክንያታቸዉን ገልጸዉ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ በጽሁፍ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ከአቀረቡ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ መጥራት አለበት
13.4 መደበኛዉ ጠቅላላ የአባላት ጉባዔ በዓመት አንዴ ይሆናል:: ኣስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግማሽ አመት ነሃሴ ውስጥ ይጠራል::
13.5 የጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ቀን ቦታና ሰዓት ተጠቅሶ የስበሰባዉ ቀን፣ ከመድረሱ 30 ቀናት በፊት የጥሪ ደብዳቤዉ በሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ለአባላት በሙሉ በቅድሚያ መላክ አለበት.
ኣንቀጽ 14 የሥራ አስኪያጅ (Executive) ኮሚቴ
14.1 የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ለማናቸዉም የማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ሃላፊነቱ በህገ ደንቡ ለሌላ የአመራር አካላት እስካልተሰጠ ድረስ ተጠያቂ ነዉ:: በተለይም የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፣የውይይት አርእስቶችን ዘርዝሮ ለጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ አባላትን ይጠራል
14.2 የጠቅላላ ጉባዔ ዉሳኔዎችን ተግባራዊ ያደርጋል
14.3 በማህብሩ ሕገ ደንብ የጸደቁ ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ እቅድና ፕላን በማውጣት ተግባራዊ ያደርጋል አፈጻጸማቸውን ለጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርት ያቀርባል.
14.4 የማህበሩን አመታዊ ባጀት ነድፎ ለጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል. በማህበሩ የገንዘብ ሁኔታና በማህበሩ እንቅስቃሴ ላይ አመታዊ ሪፖርት ያቀርባል.
14.5 በአዲስ አባላት የአባልነት ማመልካቻዎች ላይ ዉሳኔ ይሰጣል
14.6 ማህበሩ በሚያዘጋጃቸዉ ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች የመግቢያ ክፍያ ጣራ ይወስናል
14.7 አጣዳፊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ብማሰባሰብ ይተነትናል የፕሬስ መግለጫዎችን ያወጣል ፣ያሰራጫል
14.8 ከተለያዩ ተቋማት ጋር ይገናኛል፣ ትብብር ይፈጥራል፣ ውል ይፈራረማል በጠቅላላ ጉባዔው የሚሰጡ መመሪያዎችንና ውሳኔዎች ያስፈጽማል::
14.9 በስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የሚወሰነዉ ውሳኔ ህጋዊ የሚሆነዉ(ምልዓተ ጉባዔ) የአመራሩ አባላት ከግማሽ በላይ ሲገኙ ብቻ ነው::
14.10. የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባዔዉ ለ 2 የስራ ዘመን ይመረጣል:: አንድ የስራ ዘመን 2 አመት ነው::
14.11 የማህበሩ አመራሮች የስራ ዘመን ሲያበቃ አዲስ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሶስት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት በጠቅላላ ጉባዔው ይመረጣሉ ::
14.12 ማንኛዉም የኣመራር አባል በተከታታይ ለሁለት የስራ ዘመናት መመረጥ ይችላል.
14.13 ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባልነት የሚወዳደሩት እጩዎች ከምርጫዉ በፊት በምርጫዉ ለመሳተፍና ላለመሳተፍ ፈቃደኝነታቸዉን ለአስመራጭ ኮሚቴ በቅድሚያ ማረጋገጥ አለባቸዉ.::
የድምጽ አሰጣጡ እጅ በማንሳት ይሆናል እያንዳንዱ የስራ ሃላፊነት የሚወሰነዉ በጠቅላላ ጉባአዔ ነው::
ኣንቀጽ 15 የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት
15.1 የሥራ አሥኪያጅ (Executive) ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባዔ ከሚመረጡትና የአዉሮፓ ሃገራት ተወካዮች አባላት ያሉት ይሆናል:፣
የሥራ ስኪያጅ ኮሚቴ አባላት በጋራ ማህበሩን በህግ ፊትና ከህግ ፊት ዉጪ ይወክላሉ፣ ሊቀመንበሩ ኦፊሲዬላዊ የማህበሩ ተጠሪ ነው ::
15.2 የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ሊቀመንበር ምክትል ሊቀመንበር፣ ፀሃፊ ፣ ገንዘብያዥ፣የሒሳብ ሹም፣ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣የሚዲያና የማስታወቂያ ኦፕሬሽን አገልግሎት፣ያሉበት ባለሰባት የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡
15.3 ለስራው ክንውን የሚረዱ የስራ አፈጻጸም ስርዓቶች ያሰናዳል።በጠቅላላ ጉባዔው ሲጸድቅም በስራ ላይ ይውላል።
15.4 የማህበሩን ስራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣መመሪያ ያወጣል፣መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
15.5 እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው አየተገናኘ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
15.6 ለጠቅላላ ጉባዔ የስራ ክንውን ዘገባ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።ግንኙነቱ በአካል: በቴሊ ኮንፈረስ በምስል(Video Conference) በድምጽ ግንኑነት መስመሮች ( voice room conferences) ይሆናል::
15.7 ለማህበሩ ገቢ ያሰባስባል።
15.8 ቅጾችን አዘጋጅቶ ስራ ላይ ያውላል:
15.9 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እርዳታ ይሰጣል።
15.10 አስፈላጊ ኢንፎርሜሽን ለአባላት በወቅቱ አንዲደርስ ያደርጋል።
15.11 የማህበሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ይይዛል።
15.12 የማህበሩ አሰራር የሚሻሻልበት መንገድ እያጠና በቦርድ ሲፈቀድ ስራ ላይ ያውላል።
16.የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ተግባርና ስልጣን
ሰባቱ የስራአስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ተግባራትና ስልጣን ይኖራቸዋል።
16.1 ሊቀመንበር፣
16.1.1 የጠቅላላ ጉባዔውንና የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ስብሰባ በሊቀ-መንበርነትይመራል።
16.1,2 የማህበሩ ስራ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አንዲከናወን ያቅዳል፣የማህበሩን ስራ ይመራል፣አባላትን ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል።
16.1.3 በየጊዜው ለሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ የስራ ክንውን ዘገባ ያቀርባል።
16.1.4 የስራ አስኪያጅን ስብሰባ ይጠራል፣አስቸኳይ ሁኔታ ከአጋጠመ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሃሳብ ያቀርባል።
16.1.5 የወጪ ማዘዣዎችንና ደብዳቤዎችን በማህበሩ ስም ይፈርማል።
16.6 ምክትል ሊቀመንበር፣
16.6.1 ሊቀመንበሩ የማይገኝበት ጊዜ ሊቀመንበሩን ተክቶ የማህበሩን ስራ ያከናውናል።
16.6.2 ከሊቀመንበሩ ጋር በመሆን ማህበሩን ይወክላሉ::
16.6.3 ከሥራ አስኪያጅ ኮሚቴውና ከሊቀመንበሩ የሚሰጡትን ተጨማሪ ስራዎች ያከናውናል::
16.7 ጸሐፊ
16.7.1 የማህሩን አባላት የስም ዝርዝርና መዛግብት ይይዛል።
16.7.2 የጠቅላላ ጉባዔውንና የስራ አስኪያጅ ኮሚቴውን አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅድ በየወሩ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባሎችን፣በየሶስት ወር፣ ሲወሰን የማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ይጠራል።
16.7.3 የስብሰባዎችን ቃለጉባኤ ይይዛል፣ያዘጋጃል፣ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ያቀርባል።
16.7.4 የማህበሩን ጽህፈት ቤት ስራ ያከናውናል።
16.8 ገንዘብ ያዥ
16.8.1. በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለማህበሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብበ የጊዜው እየሰበሰበ በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል።
16.8.2 በመመሪያው መሰረት ማህበሩ ለአባሎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ወይም ክፍያ ቦርዱ ሲወስን ይፈጽማል።
16.8.3 ቼኮች በሁለት ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል፡፡
16.8.4 የማህበሩን ስራ ማካሄጃ በጀትያዘጋጃል፣ሲጸድቅም በስራ ላይ ያውላል።
16.8.5 ወጪዎቹ በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል።
16.9 የሂሳብ ሹም (አካውንታንት)
16.9.1 የማህበሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል።
16.9.2 የማህበሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል።
16.9.3 ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል።
16.9.4 የባንክ ደብተሮች ይይዛል፣
16.9.5. የማህበሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ያቀርባል።
16.9.6 በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል።
16.10 የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
16.10.1 በማንኛውም ማህበሩን በሚመለከት ሁኔታ የሚደረገውን የማሰተዋወቅያ ስራ ያከናውናል።
16.10.2 ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል።
16.10.3 ማህበሩን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ ጽሁፎችን አያዘጋጀ በየቦታው ይበትናል።
16.10.4 ማንኛውንም የማህበሩን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ለአባላት ያስተላልፋል ወይም መተላለፉን ያረጋግጣል።
16.10.5 የማህበሩን ዓላማ ሊያግዝ ከሚችሉ ተቋማት ሊገኝ የሚችለውን ጥቅምና እርዳታ እየተከታተለ ለስራ አስኪያጅ ኪሚቴው ያቀርባል።
16.10.6 የማህበሩን ዓላማ ለማስፈጸም ከሚያግዙ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመስረት ስለ ዝርዝር ስራቸው ለሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ሪፖርት በማቅረብ ማህበሩ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎቶች የሚያገኝበትን መንገድ ያዘጋጃል።
16.11 የማስታወቂያና ኦፕሬሽን አገልግሎት ሃላፊ
16.11.1 የማህበሩ አሰራር በሚቀላጠፍበት ሁኔታላይ አጠቃላይ ጥናቶችን እያደረገ ሪፖርቱን ያቀርባል በማህበሩ የዶሜይን(Domain) ድረገጽ(website) ይለጥፋል ።
16.11.2 ስለ ስብሰባ ቦታዎችና አጀንዳዎች፣ትራንስፖርት፣ፓሊስ፣እና ሰለመሳሰሉት ከማህሩ ስራ ጋር ሰለሚገናኙ ተቋማትና አገልግሎቶች አስፈላጊውን ጥናትና ክንውን ሪፖርት ለሥራ አስኪያጅ ኪሚቴውና አስፈላጊም ከሆነ ለአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል።
16.11.3 ማህበሩ ከጋራ ዋስትና ወይም መድሕን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ አጥንቶ ለቦርዱ ሪፖርትያቀርባል።
16.11.4 የማህበሩን ዓላማ ለማስፈጸም ያግዛሉ ተብለው የሚገመቱ ኮሚቴዎችን አዕዲቶሪያል ቦርዶችን የማቋቋም ጥረቱን በሃላፊነት ይመራል።
16.11.5 ማህበሩሕጋዊ አካልነት ለማግኘትና ይህን ይዞ ለመቆየት የሚያስፈልገውን ሁኔታ በመከታተል ስራ ላይ ያውላል።
16.11.6 የማህበሩን ድህረ-ገጽ የማቋቋሙን፣የማስተደደሩንና የማሳደጉን ጥረት በኃላፊነትይመራል።
16.11.7 የማህበሩን የ Domain (ድረገጽ) ስምያስመዘግባል፣ምዝገባውም አንዳያልፍበት በየዓመቱ አስፈላጊውን ዕድሳት ያደርጋል።
16.11.8..አባላት የማህበሩን ድህረገጽ በሚገባ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ እያጠና ለሰራ አስኪያጅ ኮሚቴው በማቅረብ ጥናቶችን ስራ ላይ ያውላል።
16.12 ኦዲተር
16.12.1 ከጠቅላላ ጉባኤው ጉባዔው ይመጥናሉ የሚባሉትን ሶስት አባላት መርጦ ኦዲተር ይሰይማል።
16.12.2 ኦዲተሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው ይሆናል።
16.12.3 ኦዲተሩ በሂሳብ ባለሙያው ተዘጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፓርት መርምሮ የደረሰበትን ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል።
16.12.3 ጠቅላላ ጉባዔው አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተር ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልል፣የወራት፣የሩብ ዓመት፣ወይም የግማሽ ዓመታት ሪፖርቶችን እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
ምዕራፍ አምስት
17. የማህበሩ የስራ ቋንቋዎች
17.1 የማህበሩ የሥራ ቋንቋዎች አማርኛ፣ እንግሊዝኛና ጀርመንኛ ይሆናሉ::
ኣንቀጽ 18. የጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት
18.1.የጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ሪፖርት በጸሃፊው ይያዛል. በስብሰባው መጨረሻ ላይ ተጠናቅሮ ከቀረበና ለጠቅላላ ጉባዔ ከተነበበ በኋላ በሊቀመንበሩና በጸሃፊው ይፈረምበታል::
ኣንቀጽ 19. የዘመን አቆጣጠር
19.1. የማህበሩ የሰራ ዘመን የሚቆጠረው በአዉሮፓውያን የሰራ ዘመን ይሆናል::
ኣንቀጽ 20. ማህበሩን ስለማፍረስ
20.1. በማህበሩ የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ተመክሮ ውሳኔ ላይ ከተደረሰ በህገደንብ አንቀጽ 13.2. መሰረት ሊፈርስ ይችላል.
20.2. ማህበሩ ሲፈርስ ወይም የማህበሩ አላማ ከህገ ደንቡ ዉጪ ሲሆን የማህበሩ ንብረት በጀርመን ሃገር ዉስጥ በሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት በኩል አዲስ አበባ
ለሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ይተላለፋል::
20.3 የማህበሩሕገ-ደንብ (Bylaw)
20.4 ይህ ሕገ-ደንብ የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ ሕገ ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
ኣንቀጽ 21. ሕጉ የሚጸናበት ጊዜ
21.1. ይህ የመተዳደሪያ ደንብ በጠቅላላ ጉባዔ ተወስኖ በጀርመን (የአውሮፓ አህጉር) የአስተዳደር ፍ/ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ይሆናል::
==============================================================================
የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ – Association of Ethiopians in Europe
The Whatsap forum chat room Guidelines of A.E.E. (Association of Ethiopians in Europe)
Inorder to use our forum or chatroom effectively as a responsible inistitution we have to put some guidlines and rule of engagements for users as follows. This draft can be changed by executive comitee of A.E.E. We hope You will enjoy it ! The chat room is managed by Ethiopian Admins from 13 European countries. A.E.E. will also regulay use Webinars and Seminars on Video Conference. We bring Ethiopian Professionals and Government officials to discuss and debate. If any violation occurs, please contact one of the admins directly. Only members can join our Video conference. Membership form is found at our webste.
Please fill up the form and submit. www.ethiodiaspora.net/membership
Chatroom and Forum Etiquette
Please note that every new user will find their first Forum post will need not to be moderated by our Forum Admin.
This is to encourage users to express themselves freely and democratically in a responsible manner .
Forum and Chatroom Rules of Engagement
Registration for the AEE Forum and Chatroom is free. However, registration means that you accept these rules of engagement. The rules are not meant to be exhaustive and we reserve the right to edit posts and/or, take other action in accordance with the purpose and principles of the Forum and Chatroom.
By registering to use Forum and/or Chatroom services, you are agreeing to be held responsible for the information you post on these services and you are confirming that you accept and understand the following Rules of Engagement
• All posts, comments and Audio messages reflect the views of the author of that post not of A.E.E..
• A.E.E will not be held responsible for the content of any member messages or information posted.
• Please show consideration and respect for other users and for their opinions.
• Be sensitive to how your messages may be viewed and perceived by others.
• Do not post in ALL CAPS or in large fonts.
• Before offering advice, make sure your information is accurate. Remember, another user’s suggestion is not a substitute for a professional’s opinion. Also, what works for you may not work for everyone.
• In accordance with policy and procedure,of A.E.E staff(admin) will delete or edit posts (this is known as “moderation”) that are deemed to be against the purpose of A.E.E Forum or Chatroom services.
Please DO NOT upload articles, images, video clips/films, or links to these, or post comments or messages which:
• are obscene, insulting or considered malicious to others;
• are disrespectful of other people’s views;
• do not reflect the purpose or theme of the specific Forum or Chatroom;
• promote political lobbying; für political groups.
• promote gambling activities;
• disclose the identity or contact details of any other person without their explicit and prior consent;
• advertise any products, websites, third parties, agencies or services without prior permission from A.E.E.
• We do not allow posts from facebook or youtube unless it is part of the discussion.
• Topics are set by Admins. So we need to focus on topic or Agenda while discussing.
• Personal Assasination or Faul Languages not allowed and anyone who violate the rule will be removed from teh forum..
Please avoid posting when under the influence of drugs or alcohol.
Any user who posts anything that may cause technical problems for A.E.E or other users will face an immediate and permanent ban from the Forum or Chatroom
Managing Your Distress
If you are feeling distressed or may be in crisis, we strongly recommend that as well as or instead of posting on the Forum, you contact our team either over the phone or via website to speak to someone who can support you.
Zero Tolerance Policy
A.E.E operates a Zero tolerance policy with regards to the abuse of other service users or staff. This is known as ‘cyber-bullying’ where it occurs online. Personal or targeted insults, threats, obscene comments and aggressive outbursts directed at other service users or at staff will not be tolerated.
Account Removal and Banned Accounts
Any user who makes ethnic based abuses or insults against on any person or grpup of people will be suspended or banned forever !
If a user wishes to leave the Forum and Chatrooms volutnatrily, we can deactivate the account at their request which means they will no longer be able to log in. Posts will remain on the site unless there are safeguarding issues, or unless a user specifically requests these to be removed.